የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ለሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ቢሮዎች ፣ኤጀንሲዎች ፣ ክፍለ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/MElU-xXqQdPznM9diBjmVvXG_GHujlT71OC-90Lft4daY5kAs4ylGTcO5iBRdmeQ7Tx6IYlbun-TwKsUcOF8sEKl8APTxXsgka32Z5Os0yY2CKFgxrXGrYAnR9J0y0A3kvPss47vBWbGsXNXxLCiS8TM9Yq_a0bVaSSp7oot35jMackitkouQkRRpAvvy_kGBEZF6pknd_gaDWrQ729VI7RkvYxVxYuzMZkXuHSZtHDmTLZClGhvTodybCXzn0MkunA_gacg6eLArOCaAJLcQQKVcZxyYIM7D2hxLBPYvFY8L7fOceh6riLMG17pO0s2riwq0RnaRivTGPLu3ZlFzw.jpg

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ለሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡

መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ቢሮዎች ፣ኤጀንሲዎች ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ውስጥ ያሉ አመራሮችን የሚያጠቃልል መሆኑንም ተነግሯል።
የጥቅማ ጥቅም መመሪያው ከታክስ ነጻ የሆነ ክፍያን፣ ቤት ለሌላቸው አመራሮች ቤት መስጠትን እንዲሁም ቤት ላላቸው አመራሮች የቤት እድሳት ወጪን መሸፈን እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማቅረብን ያካትታል። ሆኖም የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ከአመራር ውጭ ያሉ የበታች ፈጻሚዎችን አይመለከትም ተብሏል።

በብር ተሰልቶ የሚከፈለውና ከታክስ ውጭ ሆኖ በተለያየ እርከን ላሉ አመራሮች የሚሰጠው ጥቅማ ጥቅም ከፍተኛው በወር 15 ሺህ 200 ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 5 ሺህ 800 ብር መሆኑን የዋዜማ ሬድዮ ዘገባ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም ለአመራሮች በጥሬ ገንዘብ የሚሰጠው ከፍተኛው ድጎማ ስምንት ሺህ ብር አካባቢ ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ነበር። በጥሬ ገንዘብ ይሰጥ የነበረው ጥቅማ ጥቅም አሁን ላይ በእጥፍ አድጓል።

ለአመራሮች እንዲሰጥ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጸደቀው መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የማይመለሱ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ ሞባይል ስልክ እዲሁም የቤት እድሳት ወጪዎች ይገኙበታል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply