የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከ10 ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ፡፡እርምጃ የተወሰደባቸው ነጋዴዎች አላግባብ ምርት በማከማቸት ፣ ንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው በመነ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/fiuwk4YMnHKlh6EyMkXwGTFRH8Xm0JaMrRRpVPiJxUbrSjeX9wzQLdnOf13xOJfXBFJyepZLkgVuHb9JEGYMmMtYefkjHTFqIIQNs5Lv3L69K-qADuHy_rOB75vVzgG6Cxdb5yYneEarECtNh-Tf8-O2a541Cnd9pxdMDRUfGiQA95hgGaFY2wsZnKF4B_IJ-S60qiIp9v8P6rNGeFhuWJmhJ1IGBdcADLCZG25lkDnQOzeIA4cSoUT020l1FXHNJnSRJmXGWNYcMkN8LkVBoTjJ-JeONLDsqFmWDCj6BauSTSusNNHYHoVmW3M8hC6vvRfQ0NCHraYXPZay5XwWVA.jpg

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከ10 ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ነጋዴዎች አላግባብ ምርት በማከማቸት ፣ ንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው በመነገድ ፣ከዘርፋቸው ውጪ ሲነግዱ የተገኙ እና የሚሸጡትን ዋጋ ዝርዝር ባለመለጠፍ የተከሰሱ መሆናቸው ተገልጿል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ክስ ከተመሰረተባቸው ነጋዴዎች ውስጥ ከ3ሺህ በላይ የሚሆኑት የማሸግ እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑኑን ተናግረዋል፡፡

በከተማችን ውስጥ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ጫናን ከሚፈጥሩ ነገሮች አንዱ ህገወጥ ደላሎች እና ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች መበራከት መሆኑንም አንስተዋል ።

በንግድ እንቅስቃሴው ላይ የሚከሰቱትንም ችግሮች በተሻለ መልኩ ለመቅረፍ የህብረተሰቡ ትብብር ስለሚያስፈልግ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በሚያዮበት ግዜ 8588 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ጥቆማ እንዲሰጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply