You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤ ***** ንቅናቄያችን የአዲ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤ ***** ንቅናቄያችን የአዲ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤ ***** ንቅናቄያችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት «ከአንዳንድ ክልሎች የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት የመንግስትን ሥልጣን በኃይል ለመቆጣጠር ያለመ ነው» ሲሉ ሪፖርት ማቅረባቸውን ከተለያዩ ሚዲያ ዘገባዎች እና ከውስጥ ምንጮቻችን አረጋግጧል፡፡ ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ይህን መሰል እጅግ አደገኛ ከፋፋይ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ማድረጋቸው አገረ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በማናቸውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው የዓለምአቀፍ ወንጀል ጥሪ ነው፡፡ ዜጎች በነፃነት ተዘዋው…ረው የመስራት እና የመኖር ሰብዓዊ መብት ያላቸው መሆኑ ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሥምምነቶች ድንጋጌዎች እና በሥራ ላይ ባለው ሕገ-መንግስት ጭምር የተረጋገጡ ተፈጥሯዊ መብቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከንቲባዋ «የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ» እየተባለ በሚጠራው ጽንፈኛ እና በአንድ ወቅት መንግስት ራሱ «የሽብርተኞች መጠቀሚያ ነው» ብሎ በፈረጀው ሚዲያ በተከታታይ የወጡ ቅስቀሳዎች ቅጥያ የሆነ አደገኛ የወንጀል ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ዓለምአቀፍ ከተማን በከንቲባነት እመራለሁ ከሚል የመንግስት ባለስልጣን እንዲህ ዓይነት አደገኛ ቅስቀሳ በሪፖርትነት መሰማቱ እስካሁን ሲፈፀሙ ለነበሩ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች እና እየታወጀ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከለላ የሚሆን እጅግ አደገኛ የወንጀል ድርጊት ጥሪ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ትኩረት በመስጠት አስቀድሞ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ታሪካዊ ጥሪ እያደረግን፤ በተለይ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ይኼንን ባያደርግ በሩዋንዳ የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት የሚደግመው መሆኑን ማስረገጥ እንሻለን፡፡ በሌላ በኩል የፌደራል መንግስቱም ሆነ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ያደረጉትን ግለሰብ ከስልጣን እንዲያነሳ እና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ እያቀረብን፥ መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይፈፀም መንግስታዊ ማረጋገጫ ጭምር እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አዲስ አበባ፥ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም.

Source: Link to the Post

Leave a Reply