የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ26 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 29 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታና ዲዛይን ኤጀንሲ በ2013 በጀት አመት ከ26 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የያዛቸውን ተግባራት አስመልክቶ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አያሌው እንደገለጹት÷ ኤጀንሲው በበጀት አመቱ 26 ሺህ 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተሟላ ዲዛይን እና ጥራቱን በጠበቀ መሰረተ ልማት ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ኤጀንሲው በዚህ አመት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ስራ በመግባቱ ነባር ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ግድፈቶችን ለይቶ ማውጣት መቻሉን ተናግረዋል።
“የዲዛይን አለመሟላትና የውል አስተዳደር ዋነኛ ችግር እንደነበርም መለየት ተችሏል” ብለዋል።
የተጠናቀቁ በርካታ ግንባታዎች የመሰረተ ልማት ስላልተሟላላቸው ለነዋሪው ማስረከብ እንዳልተቻለም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ባለፉት ሶስት ወራት በነበረው የዝግጅት ምዕራፍ ሰራተኞችን የማደራጀት፣ ግብአቶችን የማሟላት እንዲሁም የአቅም መገንቢያ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን አቶ ቴዎድሮስ አስታውሰዋል።
በዚህም ተቋሙ እቅዱን ለማሳካት የሚያስችል አቅም መገንባቱን አብራርተዋል።
ኤጀንሲው አገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ በ2013 ዓ.ም በአዲስ መልክ ወደ ስራ የገባ መሆኑ ተነግሯል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ26 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነባ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply