የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን መዋጮ ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ጤና ቢሮዉ የህክምና አገልግሎት ከካርድ ጀምሮ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየቱ ጭማሪዉን ለማድረግ መገደዱን ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የመረጃ ባለሙያ የሆኑት አቶ አንዱአምላክ አለኀኝ፣ባለፈዉ ዓመት ለመዋጮ 1ሺህ ብር ይከፈል እንደነበር አንስተዉ የጤና አገልግሎቱ ጭማሪ በማሳየቱ የ5መቶ ብር ጭማሪ መደረጉን ነግረዉናል፡፡

ተጠቃሚዎች ለማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን የሚያዋጡት የገንዘብ መጠን ላይ ክለሳ ቢደረግም፣ ጭማሪ 5መቶ ብሩን የከተማ አስተዳደሩ የሚሸፍነዉ ነዉ ብለዋል፡፡

ተጠቃሚዎች ከፍተኛ የሚባሉ የመንግስት ሆስፒታሎች እንደ ጳዉሎስ፣ ጥቁር አንበሳ፣ አለርት እና ጴጥሮስ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት ሲያገኙ ሙሉ ወጪያቸዉ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን መሆኑንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply