
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ኮሚሽን እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝ በመቀበል ጥቁር ልብስ ለብሰው የነበሩ የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን ከስራ ገበታቸው እና ከደመወዝ አገዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋህዶ ልጆች ጾመ ነነዌን ጥቁር በመልበስ እንዲያሳልፉ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጥቁር የለበሱ ተለይተው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከመደረጉም በላይ ከስራ ገበታ እና ከደመወዝ እንዲታገዱ እየተደረገ ነው። ከሰሞኑ በደብዳቤ ጭምር መታገዳቸው ከተገለጸላቸው መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። 1) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ኮሚሽን:_ 1.1) ወ/ሮ የትናየት ተሾመ እና 1.2) ወ/ሮ ሙሉ አያሌው የተባሉ ሰራተኞች ይገኙበታል። 2) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ:_ 2.1) ወ/ሮ በለጡ ዘለቀ የተባሉ ሰራተኛ ይጠቀሳሉ። የታገዱት ባለሙያዎች ጥቁር ከመልበሳቸው ባሻገር ክልከላው ትክክል አይደለም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ማጋለጣቸው ይታወሳል።
Source: Link to the Post