በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍና የብዙሃን ትራንስፖርቱን ዘርፍ ለማጠናከር በማሰብ በአለም ባንክ አማካኝነት 160 አውቶብሶችን በተያዘው አመት ለማስገባት ግዥ ለመፈፀም ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቀዋል፡፡ ይህንን ለአሐዱ የተናገሩት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ናቸው፡፡
የአለም ባንክ የከተማዋን የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ ቁጥጥር ለማጠናከር ከ275 በላይ የሞተር ብስክሌቶችን፣ 4 አቡላንሶችንና 26 አውቶብሶችን በድጋፍ መልጅ መስጠቱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም የብዙሃን ትራንስፖርቱን ለማጠናከር ከሚያደርጋቸው ድጋፎች ባለፈ የጥናት ስራዎችንም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቀን 22/06/2013
አሐዱ ራዲዮ 94.3
Source: Link to the Post