
#የአዲስ አበባ የምክርቤት አባል የሆነችው ሀውለት አህመድ ከኦርቶዶክሳዊያን ጋር ነኝ ስትል ገለፀች። ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አብሮ-አደግ ጓደኞቼ፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ፣ የልብ ወዳጆቼ፣ የሥራ ባልደረቦቼ እና የማኅበራዊ ሚዲያ ወዳጆቼ የሆናችሁ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞች ቤተሰቦቼ:- በእውነት በዚች ቅጽበት የምትገኙበት ጭንቀትና ውጥረት እኔ ሙስሊም እህታችሁንም እየተሰማኝ ነው። መፍትሄ ከፈጣሪ እንጂ ከማን ይከጀላል? በጸሎት እንትጋ። የመጣውን በላዕ ፈጣሪ በጥበቡ ይመልሰው። የእብሪተኝነትንም ዋጋ ሲከፈል ያሳየን! በዚህ አጋጣሚ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወዳጆቻችን በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ መጽሐፌን እንደማላስመርቅና ቀኑንም ላልተወሰነ ጊዜ እንዳራዘምኩት በአክብሮት እገልፃለሁ ስትል ሀውለት አህመድ ገልፃለች። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post