የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዜጎች በጊዜዉ ወደ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ባለመምጣታቸዉ የሚሰሩት ስራ ሁሉ በግምት ሆኗል አለ፡፡ መንግስት የሚገነባቸው ትምህርት ቤ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/iX3feDQwFzQ-hJdoqdpJF4za3yENd4ynLtGoFhsbMzusKWBx6Tzq2953zzsKd3nnwdpdQ-20v6Eboy7Uz_t7n-OsJHnESNYfJXGff9PJmIOJz4zZTWpwIlEJUJY1Cfm1x6MvSplYdCBU3zn92wckP39BJYhw_OQQL1sdTSQottHpJEW-nz3gdN1uxqmto2NKFmLQjq70fYniHFFBeKQdK_c0mK7wSu2v6Jc9Xui8g4-fIXCBpG-eS_bRZknEcKINCJw_stnsuW8NMTBJQ64aXRJzL-gSzbgqALPKOUgQXGwp6fKwKgu1SKKP4cO1UfZHOJ7hO2OBoULopSIcgdRkcA.jpg

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዜጎች በጊዜዉ ወደ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ባለመምጣታቸዉ የሚሰሩት ስራ ሁሉ በግምት ሆኗል አለ፡፡

መንግስት የሚገነባቸው ትምህርት ቤቶች የሚገነቡት በሚሰበሰበው ዳታ መሰረት ልክ ነው የተባለ ሲሆን ዜጎች በጊዜ ባለማስመዝገባቸው የሚሰሩት ስራዎች ሁሉ በግምት ነው ተብሏል ።

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ጀሚላ ረዲ እንዳሉት፤የወሳኝ ኩነት ለማስመዝገብ ነዋሪዎች ወደ ተቋማት የሚሄዱት ሲያስፈልጋቸዉና ሲቸገሩ ነው ብለዋል።

ኤጀንሲው ኩነቶች በተፈጠሩበት ወቅት የማስመዝገብ ልምዳቸዉ ደካማ በመሆኑ ድርጅቱ ለተቋቋመበት አላማ በትክክል እንዳይሰራ አድርጎታል ነዉ የተባለዉ፡፡

በመሆኑ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ውጤታማ እንዲሆን ተፈሯዊና ማህበራዊ ኩነቶች ሲፈጠሩ በቶሎ የማስመዝገብ ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ተጠይቋል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ህብረተሰቡ የማስመዝገብ ባህላቸውን ሊያሳድጉ ይገባል ተብሏል ።

ዳይሬክተሯ ልደት በ90 ቀናት እንዲሁም ጋብቻ፣ ሞት፣ ፍቺ እና ጉዲፈቻን በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

ምዝገባው በዲጂታል እንደሚከናወን እና ለተመዝጋቢዎች የሚሰጡ የህትመት ግብዓቶችም ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል ፡፡

ልዑል ወልዴ

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply