የአዲስ አበባ የአከባቢ የድምፅ ብክለት ቁጥጥር ባለስልጣን የድምፅ ብክለት ባደረሱ 1ሺህ 2 መቶ 21 ተቋማት ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ።የአዲስ አበባ የአከባቢ የድምፅ ብክለት ቁጥጥር ባለስል…

የአዲስ አበባ የአከባቢ የድምፅ ብክለት ቁጥጥር ባለስልጣን የድምፅ ብክለት ባደረሱ 1ሺህ 2 መቶ 21 ተቋማት ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ።

የአዲስ አበባ የአከባቢ የድምፅ ብክለት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ላሜሳ እርምጃ ከተወሰደባቸው 1ሺህ 2 መቶ21 ተቋማት መካከል 85 በመቶ የሚሆኑት የንግድ ተቋማት ናቸው ብለዋል።

ቀሪው 15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ አየርን የሚበክሉ ፣በፍሳሽ ውስጥ ኬሚካል በሚጨምሩና ኢንደስትሪዎች ላይ መሆኑንም ሰምተናል።

በኢትዮጵያ ህገ-መንግስትና የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አዋጅ መሰረት ዜጎች ከማንኛውም የድምፅ ብክለት ተጠብቀዉ የመኖር መብት እንዳላቸዉ ይደነግጋሉ፡፡

በአካባቢ ተጽዕኖ አዋጅ ቁጥር 229/2002 እና የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 300/2002 ላይ ድንጋጌዎች ተካተዋል፡፡

ድንጋጌዉ የመኖሪያ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ቦታዎች ቀን ላይ የድምፅ መጠናቸው በቅደም ተከተል 55፣ 65 እና 75 ዴሲቤል እንዲሆን ይደነግጋል።

በዚህም ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ሊያስተካክሉ ባለመቻላቸው የድምፅ ብክለቱ በህብረተሰቡ ላይ የጤና እክል የሚፈጥር በመሆኑ ባርና ሬስቶራንት ፣የምሽት ጭፈራ ቤቶች እና የንግድ መደብሮች ላይ እርምጃው ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ከመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ ያለመስራት ለንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ለባለስልጣኑ ተግዳሮት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

በልዑል ወልዴ
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply