የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቢስ አገልግሎት ድርጅት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ትኬቶችን በሌላ ህትመት ሊተካ ነው፡፡ድርጅቱ ለበርካታ አመታት ሲገለግለባቸው የነበሩ ትኬቶችን ሙሉ በሙሉ በአዲስ ህትመት…

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቢስ አገልግሎት ድርጅት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ትኬቶችን በሌላ ህትመት ሊተካ ነው፡፡

ድርጅቱ ለበርካታ አመታት ሲገለግለባቸው የነበሩ ትኬቶችን ሙሉ በሙሉ በአዲስ ህትመት በመለወጥ ወደ ተግባር ሊገባ እንደሆነ ገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቢስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከነገ ሃሙስ ጀምሮ አዲስ ህትመቶች አገልግሎት ላይ ይውላሉ ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸው ትኬቶች ከአሁን ቀደም ከነበሩት የተለዩ እና በዋጋ ወጥነታቸው ፣በቀለማቸው እና በሚስጥራዊነታቸው የተለዩ እንዲሁም ከአሁን ቀደም ከደንበኞች ሲቀርቡ የነበሩትን ችግሮች ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

ወደ አገልግሎት የሚገቡት አዲስ ህትመቶች ወይም ትኬቶች ከነገ ሃሙስ ጀምሮ በአምስቱም ቅርጫፎች እና በሁሉም የስምሪት መስመሮች ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸው፤ ደንበኞች በኪሎ ሜትር ትራንስፖርት ቢሮ ባወጣው ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ ሲደረጉ በነበሩት የዋጋ ተመን መሰረት የታተሙ የድርጅቱ ትኬቶች በመግዛት እንዲጠቀሙ አቶ ግዛው መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም ለአገልግሎት የሚውሉ ትኬቶች ባለ አምስት ባለ አስር ባለ አስራ አምስት ባለ ሃያ እና ሃያ አምስት ብር የዋጋ ተመን ያላቸው እና በዋጋቸው ልክ የተለያየ ቀለም እንዳላቸው ህብረተሰቡ በመገንዘብ እንዲጠቀም ዋና ስራ አሰኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply