የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሶስት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመማር ማስተማር፣በምርምር፣ ሙያዊና አሳታፊ የማህበረሰብ አገልግሎቶች ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰራ መሆኑን ጠቀሟል፡፡ዩኒቨርስቲው በውጭ ሀገራት በሚገኙ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራኖቹ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ከማመቻቸት ባለፈ ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎችም የትምህርት እድሎችን እንዲያገኙ ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ከተዘጉ አለምአቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በበይነ መረብ ስርዓት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እየሰራ ነው፡፡የተወሰኑ የላቀ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች በአውሮፓ፣በአሜሪካና በተለያዩ የውጭ ሀገራት የትምህርት እድል ያገኛሉ ተብሏል፡፡

ቀን 21/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሶስት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply