የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የደም ግፊት በሽታ ስርጭት 22 በመቶ መድረሱን አስታወቀ፡፡

የደም ግፊት በሽታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ የደም ግፊት ስርጭት 16 በመቶ ሲሆን በአዲሳ አበባ ደግሞ 22 በመቶ መሆኑን ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የጤና ማጎልበት እና በሽታ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ቢሳ በወንዶች 25 በመቶ በሴቶች ደግሞ 18.8 በመቶ ነ ዉ ብለዋል፡፡

ይህም የሚያሳየው ከ5 ሴቶች 1፤ ከ 4 ወንዶች ደግሞ 1 ሰው የደም ግፊት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የተቀመጠው ቁጥርም ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩትም እድሜቸው ከ30 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል፡፡

ለችግሩ መስፋፋት እንደመንስኤ ከሚነሱ ነገሮች ወስጥ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከመጠን በላይ ጨው መጠቀም ፣በቂ ያልሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚገኙበት አቶ ጌቱ ተናግረዋል ፡፡

የአዲሰ አበባ ጤና ቢሮ በአጠቃላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችም ተጠናክረው እንደቀጠሉ አስታውቀዋል፡፡

በሐመረ ፍሬዉ
የካቲት 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply