You are currently viewing የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ጥቁር የለበሱ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞችን ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም…

የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ጥቁር የለበሱ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞችን ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም…

የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ጥቁር የለበሱ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞችን ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ኮሚሽን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተቀብላችሁ ጥቁር የለበሳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞች ሥራ መሥራት አትችሉም ከላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በማለት ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ከልክሏል። ድሬሲንግ ኮድ የሌለው መስሪያ ቤት የምትለብሱትን ልምረጥላችሁ ማለቱ አስገራሚ ነው ለሃይማኖቱ ያለውን ንቀት ያሳየ ነው ሲሉ ሠራተኞቹ ተናግረዋል። በሥፍራው ተገኝቶ ለሕዝቡ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ የነበረው አሻም ቴሌቪዥን ቀረፃውን አቋርጦ እንዲሔድ በፖሊስ ተደርጓል ብሏል ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply