የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር በቋንቋ ዙርያ ያሳለፈው ውሳኔ አረብኛን ሲያካትት ከኢትዮጵያ አልፎ በአውሮፓና ካናዳ ዩንቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የግዕዝ ቋንቋ በስርዓተ ትምሕርቱ ውስጥ አለማካተቱ ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን በደል ነው። አሁንም ማረም አለበት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቋንቋ ጉዳይ ውሳኔ የሰጠበት ስብሰባ (ፎቶ ፋና ብሮድካስቲንግ)ፖሊሲ ሕዝብ ያድናልም፣ይገድላልም። ግዕዝ በትምሕርት ቤቶች እንዲሰጥ ህዝብ መጠየቅ አለበት። መንግስትም ምላሽ መስጠት አለበት። =======ጉዳያችን=======የአዲስ አበባ ክልል አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ አበባ የሚገኙ ተማሪዎች የሚማሩትን የቋንቋ ዓይነት በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉ ዛሬ ተነግሯል። ዜናውን አስመልክቶ ፋና ብሮድካስቲንግ እንዲህ ዘግቦታል።አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን

Source: Link to the Post

Leave a Reply