የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነ

 የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነ

  አረቄ በጫነ መኪና ምክንያት በተከሰተ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረው የአዲስ -አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ከትናንት ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ 3፡30 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ፡፡
ባለፈው ሰኞ ጥር 8 ምናልባትም በክፍያ መንገዱ የመጀመሪያና ከባድ አደጋ መድረሱን በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን የገለፀው ኢንተርፕራይዙ፣ በዚህ ምክንያት የአዲስ አደማ ዋና መውጫ መንገድ እስከ ትናንትና ድረስ ለተሽከርካሪ አገልግሎት መስጠት አቋርጦ እንደነበር አስታውሷል፡፡ በኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ የሆኑት ዘሃራ መሃመድ አንዳብራሩት መንገዱ አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጎለት ከትናንት ጥር 12ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ 3፡30 ጀምሮ ለተሸከርካሪ  አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply