የአዳሩ መረጃዎች ከአሻራ ( ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) 1) መተከል ላይ ሰው መፈናቀሉን አላቆመም፡፡ ውጥረቱ እንዳለ አለ፡፡ ከቡለን ወረዳ ትናንትና ብቻ ከ 10 ሺ ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል…

የአዳሩ መረጃዎች ከአሻራ ( ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) 1) መተከል ላይ ሰው መፈናቀሉን አላቆመም፡፡ ውጥረቱ እንዳለ አለ፡፡ ከቡለን ወረዳ ትናንትና ብቻ ከ 10 ሺ ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል…

የአዳሩ መረጃዎች ከአሻራ ( ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) 1) መተከል ላይ ሰው መፈናቀሉን አላቆመም፡፡ ውጥረቱ እንዳለ አለ፡፡ ከቡለን ወረዳ ትናንትና ብቻ ከ 10 ሺ ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል፡፡ በድምሩ የተፈናቃዮች ቁጥር ከ140 ሺ በላይ ሳይደርስ እንዳልቀረ የአሻራ ምንጮች አመላክተዋል፡፡ እንደ አሻራ ትንተና ከመተከል ህዝብ 60% አካባቢ የተፈናቀለ ሲሆን፣ አጠቃላይ ከቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ህዝብ ደግሞ 30% አካባቢ ተፈናቅሏል፡፡ የተፈናቀለው አርሶአደር ስለሆነ የመኸሩ አዝመራ ሳይሰበሰብ ቀርቷል፡፡ የመንግስት አገልግሎት ከተቋረጠ ሁለት ሳምንት አልፎታል፡፡ የመተከል ኢ-መደበኛው አጥቂ ቡድን ከጉባ ወረዳ ራስጌ በሱዳን ድንበር፣በአልጣሽ ፓርክ ዙሪያ ስልጠና እያገኘ ሲሆን፣ የኦነግ ሀይልም ወለጋን ከኦሮሚያ፣ ካማሽ እና መተከል ዞን ከቢሻንጉል በነፃ ቀጠ…ናነት ለመጠቀም ተጨማሪ ጦር እያሰለጠነ እንደሆነ አሻራ ተጨባጭ መረጃ ሰምቷል፡፡ ከኦነግ ጀርባ የኦሮሚያ ብልፅግና ውስን አመራሮች ስላሉ ኦነግ በመንግስት መዋቅሩ እርዳታ እንደሚንቀሳቀስም ታውቋል፡፡ በቅርብ ቢሻንጉል እንደ ጌዲዮ እና ሀረር በኦነግ መወረሩ አይቀርም የሚሉት ምንጮች ኦነግ ወለጋን ነፃ መፈንጫ አድርጎታል፡፡ ከንፅሃን አማራዎች በተጨማሪ የኦነግ ደጋፊ ያልሆኑ የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮችም እየተገደሉ ነው፡፡ አዳሩን በሁሩ ጉድሩ ዞን በኦነግ ታጣቂዎች ጥቃት ተከፍቶ አድሯል፡፡ 2) ህወኃት በቀሰቀሰው ጦርነት አብያተክርስቲያናት እና መስጊዶች ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ ተሰምቷል፡፡ አብዛኛዎቹ የህወኃት አመራር ድል ከራቃቸው በኃላ ቄስ እና ሸህ መስለው በየቤተእምነቱ ተገኝተዋል፡፡ ቤተእምነቶችን የጦር ማከመቻ አድርገዋቸዋል፡፡ በየአርሶአደሩ ቤት ገበሬ እና የቤት ሰራተኛ መስለው ተሸሽገዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ለማደን ሲባል ጥንታዊዉ የአልነጃሽ መስጊድ፣ መቀሌ ዙሪያ ያሉ አብያተክርስቲያናት ጉዳት እንደ ደረሰባቸው እየተሰማ ነው፡፡ በርካታ የቡድን መሳሪያዎች በየቤተእምነቶች የተገኙ ሲሆን፣ የሀይማኖት አባቶች ጉዳዮን በአፅንኦት እንዲከታተሉት እየተጠየቀ ነው፡፡ የትግራይን ንፁሃን ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ማገናኘት እና የሰባዊ ድጋፍ ማድረግም ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ 3) ብልፅግና ማዕከላዊ መመሪያየ እየተከበረልኝ አይደለም ብሏል፡፡በብልፅግ ፓርቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት የተፎፎካሪ ፓርቲ ያህል ሆኗል፡፡ ከብልፅግና ራሳችንን እንነጥላለን የሚሉ እየበዙ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎም አብይ አህመድ ከአማራ አቶ አገኘሁ ተሻገርን እና አቶ አብረሃም አለኸኝን፣ ከኦሮሞ ሽመልስ አብዲሳን እና አለሙ ስሜን በዝግ ጠርተው ችግራችሁን እንድትፈቱ የተባሉ ሲሆን፣ በየክልላቸው ከትናንት ጀምሮ ውይይት ጀምረዋል፡፡ ሆኖም ግን በአማራ ብልፅግና በኩል የተረኝነት ዝንባሌ አለ የሚለው ገዥ ሀሳብ ሆኗል፡፡ በኦሮሚያ ብልፅግና በኩል የአማራን ሀይል ለመበታተን አንዱን አመራር ከሌላው፣ አንዱን አካባቢ ከሌላው የሚነጣጥሉ ተከፋይ አክቲቪስት ለመቅጠር እንዳሰቡ ተሰምቷል፡፡ አማራን ከማዕከላዊ መንግስትነት ተጋፊነት ለማውጣት በጎጥ ለመከፋፈልም ሰላይ ተሰማርቷል እየተባለ ነው፡፡ 4) የአማራ የብልፅግና አመራሮች ፊስቡክ ላይ አትፃፉ በተባሉት መሰረት ተግባራዊ እያደረጉ ነው፡፡ ፊስቡክን እንደ ጦር የሚፈሩት ዶክተር አብይ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በደቡብ ስደረሰው መፈናቀል በመፃፋቸው ብቻ ዳንሻ ህግ ማስከበር በሄዱበት ከስልጣናቸው አንስተዋቸዋል፡፡ አቶ ከውጭ ጉዳይነት ሲነሱ ለህግ ማስከበር ዳንሻ የነበሩ ሲሆን፣ መረጃውን የሰሙት በዜና ነበር፡፡ “ገዱ ፊስቡክ ላይ የሚፅፍ ከሆነም እኔ ስልጣኔን እለቃለሁ” የሚል ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውም በብልፅግናዎች ዘንድ ወግ ሆኗል፡፡ ፊስቡክ ግንኙነታችን አሻክሯል በሚል ከታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ ማንም ባለስልጣን እንዳይፅፍ በተባለው መሰረት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ታየ ደንዳዓ ብቻ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈቃድ አማራን በአካባቢ፣ በፖለቲካ አቋም እና በተለያዮ መንገድ የሚከፋፍል እና በሌላው ብሄረሰብ ዘንድ የሚያቃርን ፁሁፍ እየፃፈ ነው፡፡ የአማራ ብልፅግናዎች ግን ለታየ ደንዳዓ እንኳን መልስ ለመፃፍ አልቻሉም፡፡ 5) በሁሉም ክልሎች ኦሮሞኛን ለማስተማር ከጋምቤላ፣ ከቢሻንጉል፣ ከድሬድዋ፣ከአዲስ አበባ፣ከሀረር ክልሎች ጋር የውስጥ ስምምነት ተደርሷል፡፡ የሶማሌ ክልል ላይስማማ ይችላል በሚል ሶማሌኛን በኦሮሚያ ክልል ቀድም ማስተማር እና መደራደር በአማራጭነት ተይዞ የኦሮሚያ ክልል ሶማሌኛን ማስተማር ጀምሯል፡፡ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳድር የገዳ ትምህርት መፅሃፍ ይታተምልኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን፣ የአማራ ክልል ከዚህ ቀደም በዋግህምራ ብሄረሰብ በአበርገሌ ወረዳ ለሚኖሩ ትግረኛ ተናጋሪዎች በትግረኛ በራሱ ወጪ መፅሃፍ አሳትም ያስተምር ነበር፡፡ 6) ሱዳን 65ኛ ዓመት ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችበትን ቀን እያከበረች ሲሆን፣ በዳርፉር የነበረው 27 ሺ አካባቢ የተባበሩት መንግስታት ጦር ከ13ዓመት በኃላ መውጣቱ እና ሱዳን ከሽብርተኞች መዝገብ መሰረዟ በድል በዓሏ በስኬትነት አንስታለች፡፡ ቀጣይ ራሳችን በራሳችን ስለምንመራ ድንበራችን እናስመልሳለንም እያሉ ነው፡፡ ሱዳን ከምዕራባውያን እና ከመካከለኛው ምስራቅ የዲፕሎማሲ ድል ስለቀናት ኢትዮጵን እንደ አጋር ለማየት አልቻለችም፡፡ የኢትዮጵያ ግንኙነት ወደ ሩሲያ እና ቻይና የዞረ ስለሆነ፣ ሱዳን ከግብፅ ጋር ተዋዳለች፡፡ ይህም ለኢትዮጵያ ስጋት ሆኗል፡፡ ተጨማሪ መረጃ በዮቲዮባችን አግኙ፡፡ https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply