የአድዋን የአይበገሬነትና የድል አድራጊነት መንፈስ በመጠበቅ የሕዝባችንን ኹሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁላችንም በጋራ የምንነሳበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ አቶ በለጠ ሞላ ተናገሩ። አማራ ሚ…

የአድዋን የአይበገሬነትና የድል አድራጊነት መንፈስ በመጠበቅ የሕዝባችንን ኹሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁላችንም በጋራ የምንነሳበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ አቶ በለጠ ሞላ ተናገሩ። አማራ ሚ…

የአድዋን የአይበገሬነትና የድል አድራጊነት መንፈስ በመጠበቅ የሕዝባችንን ኹሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁላችንም በጋራ የምንነሳበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ አቶ በለጠ ሞላ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል ዛሬ ማለትም የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ራስ አምባ ሆቴል በፓናል ውይይትና በኪነጥበባዊ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበሩን አስታውቋል። የአድዋን ድል በዓል ስናከብር አድዋ ትውስታ ብቻ ሳይሆን በታሪክ አምድነቱ የአባቶቻችንን የአይበገሬነት፣ የድል አድራጊነት እንዲሁም የአገረ መንግስት ግንባታ አበርክቶት የምንዘክርበት ነው ያሉት የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ ሕዝባችን ከተጋረጠበት አደጋ ብሎም አገራችን ከገባችበት አዘቅት ለማውጣት ልክ እንደ አድዋው ሁሉ ዛሬም በጋራ መነሳት፣ በብልኃትና በጥበብ መሥራት አለብን ብለዋል። አቶ በለጠ አክለውም አብን ታሪክን ከመጠበቅ ባለፈ ሕዝባችንን የሥልጣን ባለቤት ሆኖ በአገሩ ላይ በእኩልነትና በነፃነት እንዲኖር በማድረግ ታሪክ ለመስራት ጊዜው አሁን ነው በሚል መንፈስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዝግጅቱ ላይ የአድዋ ድልና ቱርፋቶቹ፣ የአድዋና የታሪክ ተቃርኖ እንዲሁም ትውልዱ ከአድዋ ታሪክ ሊማር የሚገባቸው ነገሮችን በተመለከተ የውይይት መነሻ ኃሳብ በአብን የውጭና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማሪያም ቀርቧል። አድዋ እናትና አባቶቻችን በጥበበኞቹ መሪዎቹ እምዬ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ እየተመሩ ጭቆናና ግፍ ላይ ዘምተው ድል የተቀናጁበትና ነፃነትን ለትውልድ ያወረሱበት ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የዚህ ዘመን ትውልድም ሕዝባችን የሚደርስበትን መዋቅራዊ ጭቆና በመስበር በእኩልነትና በፍትኅ የሚኖርበትን ሥርዓት እውን በማድረግ የአባቶቹ ልጆች መሆኑን ማስመስከር አለበት ብለዋል። በቀረበው የመነሻ ጽሁፍ ላይ ከተሳታፊዎቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply