የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ ወታደራዊ ሹማምንትና ሚዲያዎች እንዲሁም ሀገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ ወጣ፡፡…

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ ወታደራዊ ሹማምንትና ሚዲያዎች እንዲሁም ሀገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ ወጣ፡፡…

የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ ወታደራዊ ሹማምንትና ሚዲያዎች እንዲሁም ሀገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ ወጣ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-18/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ ወታደራዊ ሹማምን ት በፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የጁንታው ህወሃት ቡድን አባላትና በአሃገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱ ተገልጻል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ የእርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል። በዚህምመሠረት፡- 1. ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን 2. ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣይ 3. ኮሎኔልገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ 4. ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል 5. ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን 6. ኰሎኔል ጌትነት ግደያ 7. ኮሚሽነር ረታ ተስፋዬ ናቸው። በተያያዘም ቀደም ሲል የነበራቸው ወታደራዊ ኃላፊነት እና ከጁንታው የህወሃት ቡድን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ትስስር ተጠቅመው ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል በመንግሥት ላይ በመፈፀም ከፍተኛ ንብረት ማካበታቸው የተደረሰባቸው 20 ግለሰቦች ስማው ቀጥሎ ተገልጿል። በዚህም መሰረት፦ 1. ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ- ሥልጠና ዋና መምሪያ ጡረተኛ 2. ሜጀር ጄነራል ገብረገአድሃና ገብረዲላ- መረጃ ዋና መምሪያ ጡረተኛ 3. ሜጀር ጄነራል ተክለበርሃን ወልደአረጋይ /ሳንቲም/ – የኢንሳዳይሬክተር ጡረተኛ 4. ሜጀር ጄነራል ብርሃነ ነጋሽ /ወዲመድን/ – ሚንስትር ዴኤታ ጡረተኛ 5. ሜጀር ጄነራል ማዕሾ በየነ- ምሥራቅ ዕዝ አዛዥ ጡረተኛ 6. ሜጀር ጄነራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል- ሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ጡረተኛ 7. ሜጀር ጄነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ – ማዕከላዊ ዕዝአዛዥ የነበረ ጡረተኛ 8. ሜጀር ጄነራል ነጋሲትዕኩ- በሰላም ማስከበር ግዳጅ የከዳ 9. ብርጋዴር ጄነራል አባዲፍላንሳ- ምስራቅ ዕዝ መረጃኃላፊ ጡረተኛ 10.ብርጋዴር ጄነራል ፀጋየ ተሰማ /ፓትሪስ/- ኢንስፔክሽን ዋና መምሪያ የነበረ ጡረተኛ 11 ብርጋዴር ጄነራል ምግበ ኃይለ- ሥልጠና ዋናመምሪያ ጡረተኛ 12. ብርጋዴር ጄነራል ተክላይ አሸብር /ወዲአሸብር/- የንዑስ ዕዝ አዛዥ የነበረ ጡረተኛ 13. ብርጋዴር ጄነራል ኃይለሥላሴግርማይ /ወዲዕበይተ/- ዘመቻ ዋና መምሪያ ጡረተኛ 14. ብርጋዴር ጄነራል ሙሉጌታ በርሔ- የአጋዚ ክፍለ ጦአዛዥ የነበረ ጡረተኛ 15. ኮሎኔል ተወልደ ገብረተንሳይ- መከላከያ መረጃ ጡረተኛ 16. ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ – መከላከያ መረጃ የነበረ ጡረተኛ 17. ኮሎኔል ደጀን ግርማይ- የዕዝ ስምሪት ኃላፊ ጡረተኛ 18. ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል- የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ጡረተኛ 19. ኮሎኔል ገብረሀንስ አባተ /ወዲአባተ/- ምዕራብ ዕዝ 43ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ጡረተኛ የነበረ 20 ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን /ወዲአድዋ/- ድሬዳዋ ያለ ቀደም ብሎ የወጣ ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረቶች ማስመለስ ይቻል ዘንድ ንብረቶቹ የሚገኙበትን ትክክለኛ አድራሻ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ቢሮ ስልክ ቁጥሮች፥ 011 1 55 12 00 ወይም የነፃ የጥሪ መስመር 861 ወይም በአካል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት እንድታሳውቁን የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብሏል የፌደራል በመግለጫው። እንዲሁም በአገር ውስጥና በውጪ አገር ተቀምጠው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም አገር በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማሩ፦ 1. ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ 2. ዶክተር አወልአሎ ቃሲም 3. ዶክተር ኢታና ሀብቴ 4. ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ 5. አቶ ዳንኤል ብርሃኔ 6. አቶ ፍፁም ብርሃኔ 7. አቶ አሉላ ሰለሞን 8. ሠናይት መብርሃቱ በፈፀሙት የአገር ማፍረስ ወንጀል በሕግ የሚፈለጉ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply