You are currently viewing #የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዘገብ ድጋፍ ተጠየቀ! ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣  በየዓመቱ የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል በዩኔስኮ የዓለም ቅ…

#የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዘገብ ድጋፍ ተጠየቀ! ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በየዓመቱ የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል በዩኔስኮ የዓለም ቅ…

#የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዘገብ ድጋፍ ተጠየቀ! ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በየዓመቱ የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ለማስመዘገብ ሁሉም የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ተጠየቀ። በአገር አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበውን የዘንድሮ አገው ፈረሰኞች በዓል ማህበሩ ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁን አስታውቋል። ማህበሩ ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን የ83ኛውን የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል ቅድመ ዝግጅትን አሰመልክተው በሰጡት መግለጫ ማህበሩ የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ሁሉም አካላት ድርሻውን እንዲወጣ ጠይቋል። የአዊ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንግዳ ዳኛው በዓሉ የሁሉም ዜጋ በመሆኑ በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የማህበሩ ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ ከ62 ሺሕ በላይ አባላት እንዳሉት ገልፀው በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በበዓሉ ላይ እንዲታደሙም ጥሪ አቅርበዋል። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋረዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት ማህበሩ የአገው ህዝብ አምባሳደርና የህዝቡ መገለጫና ምልክት እየሆነ መጥቷል። የአገው ፈረሰኞች ማህበር የአድዋ ጀግኖችና ፈረሶቻቸውን ለማስታወስ በጥቂት አባላት ከ83 ዓመት በፊት መቋቋሙ ተገልጿል ሲል ኢፕድ ዘግቧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply