የአገው ፈረሰኞች ማህበር የአገውን ህዝብ ባህልና ትውፊት በማስተዋወቅ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም‼️ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር…

የአገው ፈረሰኞች ማህበር የአገውን ህዝብ ባህልና ትውፊት በማስተዋወቅ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም‼️ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር በደቡባዊ ምዕራብ አቅጣጫ በ122 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የብሔረሰብ ዞኑ መቀመጫ የሆነችው እንጅባራ ከተማ ደግሞ ከአዲስ አበባ ባህርዳር መንገድ በ435 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መገኛዋ ነው።የአዊ ዞን አስተዳደር በምስራቅ- የምዕራብ ጐጃም ዞን፣ በምዕራብ- የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በሰሜን- የሰሜን ጎንደርና ምዕራብ ጐጃም ዞኖች፣ በደቡብ- ምዕራብ ጐጃምና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ያዋስኑታል።የአዊ ብሔረሰብ ዞን የበርካታ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህብ ሀብቶች፣ የባህል እሴቶችና ማህበራዊ ኩነቶች ባለቤት ነው። ፧ የተለያዩ ውሃማ አካሎች በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ትልልቅና መለስተኛ ወንዞች፣ ምንጮች፣ እርጥበት አዘል ባህር ሸሸ መሬቶች፣ ፏፏቴዎችና ሐይቆች የተመልካችን ቀልብ ሊስቡ የሚችሉ ውብና ማራኪ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች መገኛ ነው።ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ በርካታ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት፣ መካነ-መቃብሮችና ዋሻዎች፣ የብራና መጽሐፍት እንዲሁም ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደኖች፣ በርካታ የዱር እንስሳትና አዕዋፍ ዝርያዎች መገኛ ነው። ለአብነት የዘንገናና የጥርባ ሃይቅ፣ የትስኪ፣ የዶንደር፣ የፋንግና የጋርቾ ፏፏቴ፣ የዳንጉላ ዋሻና የወለተ ጴጥሮስ ገዳምን በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል።ብሔረሰቡ ተቀድቶ የማያልቅ ባህል፤ የራሱ ቋንቋና በኢትዮጵያ ታሪክ አስተዳደራዊ ድርሻ የነበረው ቀደምት ህዝብ ነው፡ ፧ የአገው ፈረሰኞች ማህበር የብሔረሰቡን ባህልና ትውፊት በማስተዋወቅ ረገድ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡ በ1932 ዓ.ም ከነበረው የጣሊያን ወረራ ጋር ተያይዞ በጊዜው ፈረሰኛው ያበረከተውን አስተዋጽኦ ለመዘከር በጥቂት አባላት የተመሰረተ አንጋፋ ማህበር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ60ሺ በላይ አባላት አሉት። በዓሉ በየአመቱ ጥር 23 በታላቅ ድምቀት ይከበራል።በእለቱም የፈረስ ሸርጥ፣ጉግስና ስግሪያ ስርአቶች ይከናወናሉ። ከመሰረተ ቀበሌ እስከ ዞን የራሱ የሆነ አደረጃጀትና የስልጣን መዋቅር ያለው ሲሆን በየ5 አመቱ የሚመረጡ አስር አስር የኮሚቴ አባላት አሉት። የማህበሩ ከዋና አላማው በተጓዳኝ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች የሚፈቱበት ፣የሚረዳዱበት የሚተጋገዙበት ጭምርም ነው። ፧ ማህበሩ ከምንም አይነት ከመንግስት ፣ከሀይማኖትም ይሁን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሲሆን አባል ለመሆን ምንም አይነት የእምነት ፣የፆታ፣የማህበራዊ ደረጃ፣ የብሔር ፣የፖለቲካ ልዩነት የለውም ። ይህ በዓል በማህበረሰቡ ብቻ በድምቀት ሲከበር የቆየና አሁንም እየተከበረ ያለ ሲሆን በተለይም ከ78ኛው በዓል ጀምሮ በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም በ አገው ፈረሰኞች ማህበርና በብሔረብ አስተዳደሩ ትብብር በበለጠ በድምቀት እየተከበረና በሀገር አቀፍ ደረጃም ታዋቂነት እያገኘ የመጣ ተወዳጅ በዓል ነው። 83ኛ ዓመቱንም ጥር 23/2015 ዓ.ም ከፌደራልና ከክልል የመጡ እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ የፈረስ ትሪቶች በእንጅባራ ከተማ ለማክበርና በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ፧ አንድ ሰው ፈረሰኛ ለመባል ፈረስ፣ ኮርቻ፣ ፋርኒስ፣ ለኮ፣ ወዴላ፣ ምቹና ግላስ ለፈረሱ ያስፈልገዋል። ለራሱ ደግሞ አለንጋ፣ ዘንግ፣ ገንባሌ፣ ሳርያን ኮት፣ ጀበርና ሊያሟላ ይገባል። ጦር፣ ጋሻና ሌሎች የአባቶቻችን የዘመቻ ቁሶች ካሉት ደግሞ ተመራጭ ነው።አገውና ፈረስ ተለያይተው አያውቁም ወደፊትም አይለያዩም። በአገዎች ዘንድ ፈረስ የታመመን ወደህክምና ያደርሳል፤ የተጋቡ ጉብሎችን ያንሸራሽራል፤ በዓልና ሃዘንን በማድመቅም ትዝታው እንዲታወስ ያደርጋል። ፈረስ መሬቱን አርሶ ጎተራ ሙሉ እንዲሆን ያደርጋል። በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ማጓጓዣ ሆኖም ያገለግላል። ለእነሱ ፈረስ ሁሉም ነገራቸው ነው ማለት ይቻላል። የአገው ፈረሰኞች ማህበር የብሔረሰቡን ትውፊት በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ፧ ጀምስ ብሩስ የተባለ ስኮትላንዳዊው አሳሽ ስለ አዊ አገዎች እንዲህ ሲል ይገልፃል “አባዊ”በሚባል ስም የሚጠራ ታወቂው የናይል ወንዝ “ሰከላ”ከሚባል የአገዎች ሀገር እንደሆነ ጀምስ ብሩስ አስረድቷል።ይህ አሳሽ የአዊዎችን ወታደራዊ ብርታትን ከመሰከሩ የአይን እማኞች አንዱ ነው።ተመራማሪው በአንድ ወቅት አገዎች እጅግ ጠንካራና አይበገሬ እንደነበሩ ከመመስከሩም በላይ በዚያን ጊዜ እንኳን ጠላት ቢመጣባቸው ከ400 በላይ ፈረሰኛና በርካታ እግረኛ ጦር በአንዴ ማንቀሳቀስና ጠላትን ወደ መጣበት እንደሚመልሱና መደምሰስ ይችሉእንደነበር በአይኑ እንዳየ ፅፎል።ለዚህም ምሳሌ ሲሰጥ “ዚጋሚ”ብቻውን ከአፄ ሱስንዮስ (1565-1632)እስከ ታላቁ እያሱ(1682-1796) ዘመናት ድረስ በታከታታይ የተሰነዘሩበትን ጦር የወረራ ዘመቻ ዚጋሞች በአስደናቂ ሁኔታ በመከላከል ማንነቱን አስከብሮ እስከ 18ኛው ክፍለዘመን ድረስ ቆይቷል ይላል።ዳንግሊ የተባላው አገውም እንዲሁ ጠንካራ የተባሉትን የዘመኑ ነግስታት ማለትም የአፄ ፋሲለደስን፣የፃዲቁ ዮሐንስና ዳግማዊ እያሱን የወረራ ዘመቻዎች በመከላከል እስከ 18ኛው ክፍለዘመን ድረስ ነፃነቱን ጠብቆእንደቆየ ብሩስ አክሏል ።ወደ አቸፈር እና ቡሬ በተባሉ ቦታዎች አገዎች የሰርፀ ድንግልን እና የአፄ ሱስንዮስን በርካታ ጦር ክፉኛ ጎድተውና አሳፍረው መልሰውታል ይላል ስኮትላንዳዊው አሳሽ ጄምስ ብሩስ፡፡ ጥር 23/2015 ዓ.ም እንጅባራ እንገናኝ ሰላም ! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply