You are currently viewing የአገዛዙ ጦር በወግዲ ወረዳ በጎረንጅ፣ በጎለሌ፣ በአጋምሳ እና በያጌ የአርሶ አደሩን መሳሪያ በመንጠቅ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ወቀሱ።        አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የአገዛዙ ጦር በወግዲ ወረዳ በጎረንጅ፣ በጎለሌ፣ በአጋምሳ እና በያጌ የአርሶ አደሩን መሳሪያ በመንጠቅ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ወቀሱ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የአገዛዙ ጦር በወግዲ ወረዳ በጎረንጅ፣ በጎለሌ፣ በአጋምሳ እና በያጌ የአርሶ አደሩን መሳሪያ በመንጠቅ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ወቀሱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ በጎንጅ እና በጎለሌ አካባቢ ነዋሪዎች እና ፋኖዎች ላይ ከሰሞኑ ተኩስ የከፈተው የአገዛዙ ጦር ዙ23፣ ዲሽቃ እና ሌሎች መሳሪያዎችን ሁሉ ተጠቅሟል። በተለይ ሀምሌ 9/2015 አመሻሽ ፋኖን አገኛለሁ በሚል እሳቤ በአርሶ አደሮች ላይ ጭምር ዙ 23 በተደጋጋሚ መተኮሱን ተከትሎ ጉዳት ለመቀነስ ሲባል ስልታዊ ማፈግፈግ መደረጉ ተገልጧል። ይህን ተከትሎ በጎረንጅ፣ በጎለሌ፣ በአጋምሳ እና በያጌ በመከላከያ ስም የገባው የአገዛዙ አፋኝ ጦር የአርሶ አደሩን መሳሪያ በመንጠቅ ድብደባ እየፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ወቅሰውታል፤ ከዚህ የከሰረ አካሄዱ በአስቸኳይ እንዲቆጠብም አሳስበዋል። የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ህዝብን በኃይል እረግጦ ፣ በመግደል እና ማዳበሪያ እየነፈጉ በኢኮኖሚ በማድቀቅ ለመግዛት የማይቻል መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል ሲሉ ገልጸዋል። አገዛዙ የከፈተበትን ጦርነት ተከትሎ ህዝባዊ ኃይሉ_ፋኖ እና ነዋሪው ራሱን ለመከላከል የሰጠውን የአጸፋ ምላሽ ተከትሎ የሞተው እና የቆሰለው እንዳይታወቅበት ወግዲ ላይ አናሳክም በማለት በርካታ ቁስለኞችን ሲያጓጉዝ መዋሉን ነው የዐይን እማኞች ለአሚማ የተናገሩት። በተያያዘ ግን በባንዳነት የሚያገለግሉ አካላት የህዝባዊ ኃይሉን አባላት ለማስያዝ መረጃ እየሰጡ ነውና ከዚህ ጸረ አማራ አሳፋሪ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡ የሚል ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply