የአግሮፉድና የፕላስቲክ ህትመት ማሸጊያ ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡ የንግድ ትርኢቱ በጀርመኑ ታዋቂ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ፌር ትሬድ እና በኢትዮጵያው ፕራና ኢቨንትስ ትብብ…

የአግሮፉድና የፕላስቲክ ህትመት ማሸጊያ ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡

የንግድ ትርኢቱ በጀርመኑ ታዋቂ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ፌር ትሬድ እና በኢትዮጵያው ፕራና ኢቨንትስ ትብብር ለ4ኛ ጊዜ እንደሚካሄድም ታውቋል።

ዝግጅቱ ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን፣ በአግሮ ፉድና እና እሴት ሰንሰለቱ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከተለያዩ አገራት የተዉጣጡ ዓለምአቀፋ የዘርፉ መሪዎች ለኢትዮጵያ የገበያ ፍላጎት የተዘጋጁ የግብርና፣የምግብ እና የመጠጥ ማቀናባበሪያ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡበት ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈ የፕላስቲክ ህትመት እና ማሸጊያ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎችን በመያዝ፣ከ2ሺህ በላይ ለሚሆኑ ጎብኚዎች እንደሚያቀርቡም አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

በዚህ የንግድ ትርኢት ላይ፣ ከኢትዮጵያ ፣ከፈረንሳይ፣ከጀርመን ፣ከህንድ፣ከጣሊያን ፣ከኩዌት ፣ከናይጄሪያ ፣ከሩሲያ ፣ከደቡብ አፍሪካ ፣ከቱርክ እና ከአሜሪካ የተዉጣጡ ተሳታፊ ድርጅቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠብቃል ።

በአባቱ መረቀ

መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply