የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ የሽኝት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለኢትዮጵያዊ አንድነት…

የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ የሽኝት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለኢትዮጵያዊ አንድነት እስከ ህይወት መሰዋእትነት የታገሉት የአፄ ቴዊድሮስ የሹሩባ ፀጉር ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ታህሳስ 24/2014 ዓ.ም የሽኝት ፕሮግራም ይካሄዳል። የፕሮግራሙ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ እንደገለፁዉ የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ የሽኝት ፕሮግራም ከብሔራዊ ሙዚየም 2:30 ተነስቶ በእግር ወደ 4 ኪሎ አደባባይ በማርሽ ባንድና በአባት አርበኞች ይታጀባል። እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣ ሀገር ወዳድ ግለሰቦች በተገኙበት ስነ ስርዓቱ ይካሄዳል። ከ4ኪሎ አደባባይ ከተሸኘ በኃላ ጉዞ ወደ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፖርት በማድረግ የሽኝት ፕሮግራሙ እንደሚጠናቀቅ አስተባባሪ ኮሚቴዉ ገልጿል ሲል የዘገበው የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply