የአፈር ጥበቃ ስራን በዘለቄታ ለመስራት የሚረዳ ሊቁ የተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያ ይፋ ሆኗል፡፡እንጫወት ጌምስ ኃ/የተ/የግ/ማ “ሊቁ” የተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያ ከጂ.አይ.ዜድ እና ከግብርና…

የአፈር ጥበቃ ስራን በዘለቄታ ለመስራት የሚረዳ ሊቁ የተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያ ይፋ ሆኗል፡፡

እንጫወት ጌምስ ኃ/የተ/የግ/ማ “ሊቁ” የተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያ ከጂ.አይ.ዜድ እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ይፋ አድርጓል፡፡

ሊቁ በጨዋታ መልክ የቀረበ የአፈር ጥበቃ ስራን በዘለቄታ ለመስራት የሚረዳ መተግበሪያ ነው፡፡

ሊቁ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተጫዋቾች ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

መተግበሪያው በጎ መንደር የተሰኘ ቦታ እንዳይጠፋ ለማድረግ ተጫዋቾች በሚያደርጉት ጥረት የአፈር ጥበቃ ግንዛቤን ያዳብራል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሊቁ የዲጂታል መተግበሪያን ያለምንም ከፍያ ከጎግል ፕሌስቶር ላይ ማውረድ የሚቻል ሲሆን ጨዋታውን ባሸነፉ ቁጥር ግንዛቤ እና ችሎታን የሚጨምሩ የዲጂታል ሽልማቶችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡

መተግበሪያዉ የአፈር ጥበቃን በበቂ ሁኔታ ያስገነዝባል  የተባለ ሲሆን፤ለአፈር ጥበቃ የሚረዱ የተለያዩ መንገዶችን እንደ ዛፍ መትከል ፤ እርከን፤ ክትር መከተር የመሳሰሉትን ተግባራት በጨዋታው በመተግበር በቂ ግንዛቤን እንደሚሰጥ ተነስቷል፡፡

ሌላኛዉ በጎ መንደርን ማዳን ሲሆን በጨዋታው በጎ መንደር የተሰኘው ምናባዊ ስፍራ የሚጠፋ ሲሆን ተገቢው እንክብካቤ ባደረጉ ቁጥር ይህንን ምናባዊ ስፍራ መታደግ የሚችሉ ይሆናል፡፡

በጨዋታዉ ከሚገኙ ጉዳዮች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ ደግሞ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ጀግንነትን መጎናፀፍ ነዉ፡፡

በጨዋታው የሚያገኙትን የግንዛቤ እና የክህሎት ሽልማቶቸ በመጠቀም ባሸነፉ ቁጥር በስተመጨረሻ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ጀግና የሚል ስያሜን እንደሚያገኙም ተነግሯል፡፡

እንጫወት ጌምስ ኃ/የተ/ግ/ማ የጌም ዴቨሎፕመንት ተቋማት አንዱ ሲሆን ባለፉት አመታት እንደ ማሞ ጉዞ፣ግዕዝ፣ ሴና ፈርዳ፣የመስቀል ወፍ የመሳሰሉ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ አድርሷል።

በእስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply