የአፋርና የአማራው ሕዝብ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ይብቃህ!! የግጥሙ ጸሐፊ፡ ይፍሩ ኃይሉ ======================= ግራ ቀኝ ተከባ ኢትዮጵያ በጠላት:… አገር በቀል ባንዳ : ጁ…

የአፋርና የአማራው ሕዝብ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ይብቃህ!! የግጥሙ ጸሐፊ፡ ይፍሩ ኃይሉ ======================= ግራ ቀኝ ተከባ ኢትዮጵያ በጠላት:… አገር በቀል ባንዳ : ጁንታ ተነስቶባት: ያልዘራችው አረም :ከመሃል በቅሎባት: ወዳጄ ያለችው ዛሬ :ተንሸራቶ: ያተራምሰናል መሃላችን ገብቶ:: ጁንታ የሚሉት ባንዳ:የተክለፈለፈ: እንዳበደ ዉሻ ነክሶ እየለከፈ: ኧረ ስንቱ አለቀ : ስንት ሕይወት አለፈ! ባልቴት;ሽማግሌ:አዋቂ ልጅ አይል ሕፃናትን አርዶ :እርጉዝ የሚገድል: ቤተ ዕምነት አጋይቶ መስኪድ የሚያቃጥል: ቅዱሳት መጻሕፍት: ቁርዓን አርክሶ:ቀዶ ‘ሚፀዳዳ: እሬሳ ‘ሚቀብር ባደርበት እልፍኝ:በተኞበት ጏዳ: በበላበት መሶብ : በተኛበት አልጋ :ፍራሽና አንሶላ: እበቱን ቆልሎ: ከዚያው የሚበላ: እርኩስ አረመኔ: ለዓይን የሚያስጠላ:: ያገርህ ነቀርሳ ዳግም አንሰራርቶ ፊቱን እንዳይመልስ ዳግም ጦር አንስቶ: ጠላትህ ወያኔ:ሞቱን የምታውቀው: ገድለህ ስትቀበረው: ወይ ክንዱን ጠምዝዘህ ለፍርድ ስታቀርበው: አርሰህና አምርተህ:ነግደህ: አትርፈህ: ወልደህና ከብደህ:በልፅገህ አልፎልህ: መኖር የምትችለው በሰላም ባገርህ ያን ጊዜ ብቻ ነው ሰላምና ዕረፍትህ:: በሕይወት እያሉ ጁንታና ወያኔ: ሰላም አታገኝም እወቀው ወገኔ:: እንቅልፍ አይገኝም ከዛፍ ላይ ተኝቶ: መሰበር አለና ወድቆ ተንክታክቶ::

Source: Link to the Post

Leave a Reply