የአፋር እና የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ግንኙነቶቻቸውን እንደሚያጠናክሩ አስታወቁ

የአፋር እና የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ግንኙነቶቻቸውን እንደሚያጠናክሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፋር ክልል እና የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ ግንኙነቶቻቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለፁ፡፡

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስትራቴጂክ አመራሮች በድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተገኝተው የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል::
በልምድ ልውውጡ የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ማኦ ተሾመ፣ ምክትል ኮሚሽነር ጉሌድ ድርዬ እና ሌሎች አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩም በኮሚሽኑ ውጤት የተገኘባቸው የስራ መስኮችና የአፈፃፀም ሂደቶቻቸው ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚሁ የልምድ መጋራት መድረክ ማጠቃለያ ላይ የሁለቱም ፖሊስ ኮሚሽን ስትራቴጂክ አመራሮች በሰጡት አስተያየት በቀጣይም በአፋርና በድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች መካከል ያለውን ተቋማዊ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በጋራ ይሰራል ብለዋል::

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአፋር እና የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ግንኙነቶቻቸውን እንደሚያጠናክሩ አስታወቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply