የአፋር ክልል መስተዳድር የሕወሓት አማጽያን በተቆጣጠሩባቸው አካባቢዎች ሕጻናት እና አረጋውያንን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው ሲል ከሰሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀም…

የአፋር ክልል መስተዳድር የሕወሓት አማጽያን በተቆጣጠሩባቸው አካባቢዎች ሕጻናት እና አረጋውያንን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው ሲል ከሰሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአፋር ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት አማጽያኑ አሁንም ድረስ አራት የክልሉን ወረዳዎች በቁጥጥር ስር አድርገው ጥቃት እያደረሱ ነው። ጥቃቱን ተከትሎም ከ75,000 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አቶ አህመድ ገልጸው፤ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ጥቃቱን ለመከላከል እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እያለ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ 725 ተማሪዎች በሁለት ዙር ተጓጉዘው ሰመራ ከደረሱ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መሸኘታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ከትግራይ ክልል ለመውጣት ከተማሪዎቹ ውስጥ እስከ ሦስት ቀናት በእግር የተጓዙ እንዳሉ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንድ የተማሪ ወላጅ ተናግረዋል። ልጆቻቸው በትግራይ ክልል የሚማሩ ወላጆች ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ተቋማት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ቢሮ በመሄድ ልጆቻቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲፈልጉላቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር ሲል ኢትዮ መረጃ ኒውስ አስነብቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply