
ዳካር ሴኔጋል ውስጥ በተካሄደው በስምንተኛው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ውድድር ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሙዚቃ ባለሙያዎች በዕጩነት ቀርበው የተወሰኑት ሽልማቱን አግኝተዋል። ከእነዚህም መካከል ወጣቶቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች ካሥማሠ እና ጉቱ አበራ ይጠቀሳሉ። ሁለቱም ወጣት ሙዚቀኞች በአፍሪማ ሽልማት ላይ በተወዳደሩበት ዘርፍ አሸናፊ በመሆናቸው በጣም ደስታ እንደተሰማቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Source: Link to the Post