የአፍሪካ ሃገራት ለሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀረበ

የአፍሪካ ሃገራት ለሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪና መከላከያ ማዕከል ሃገራት ለሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀረበ፡፡
 
የማዕከሉ ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ በአህጉሪቷ በኮሮና ቫይረስ የሚያዘው ሰው ቁጥር እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡
 
በአህጉሪቷ በሐምሌ ወር ጨምሮ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየቀነሰ መሄዱን ገልጸዋል፡፡
 
ይሁንና በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ወረርሽኙን ለመከላከል ሃገራት የመለየት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ፣ የመመርመር አቅማቸውን እንዲጨምሩ እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በአህጉሪቷ እስከ ትናንት ድረስ 1 ሚሊየን 748 ሺህ 335 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 42 ሺህ 151 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን እንዳጡ የማዕከሉ መረጃ ያሳያል፡፡
 
 
ምጭ፡-ሲጂቲኤን

The post የአፍሪካ ሃገራት ለሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀረበ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply