የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለዉ ዉጥረት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጠይቀዋል፡፡የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በሁለቱ አገራት የተፈጠረዉን ዉጥ…

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለዉ ዉጥረት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጠይቀዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በሁለቱ አገራት የተፈጠረዉን ዉጥረት አገራቱ በተረጋጋ እና የጋራ በሆነ መንፈስ እንዲፈቱት ጠይቀዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በሰጡት መግለጫ ሁለቱ አገራት ያላቸዉን መልካም ግንኙነት የሚያበላሽ ምንም ዓይነት ዕርምጃ ከመዉሰድ እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገዉ የባሕር በር ስምምነት በሶማሊያ በኩል ተቀባይነትን እንዳላገኘ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ ምንም”የተጣሰ ሕግ” እንደሌለ ቢገልጽም፤ ሶማሊያ በበኩሏ ሁለቱ አገራት የደረሱበት ስምምነት “ሉዓላዊነቴን የጣሰ” እና “ዋጋ ቢስ” የኾነ ስምምነት ነው በማለት አውግዛዋለች።

በዚህም የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ ከሰሞኑ በኢትዮጵያና ሱማሊያ ግንኙነት ዙሪያ ያወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ ያደላ ነዉ ፤የሱማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጣሷን አላወገዘም በሚል እንደማትቀበለዉ አሳዉቃለች፡፡

ዋና ጸሀፊዉ “ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ መግለጫቸውን እንዲሰርዙና እርማት እንዲሰጡም ነዉ ” የጠየቀችዉ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም የህብረቱ አገራትን አንድነት፣ግዛት እንዲሁም ሉዓላዊነት ማክበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ያለዉን ጥሩ ጉርብትና ለሰላም፣ ለደህንነት እንዲሁም የተረጋጋ ከባቢ ለመፍጠር መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አክለዉም ሁለቱ አገራት ከሰሞኑ በተፈረመዉ ስምምነት ዙሪያ የተፈጠረዉን የሃሳብ ልዩነት ለመፍታት በፍጥነት ወደ ንግግር መምጣት አለባቸዉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የሊቀመንበሩ መግለጫ ከሰሞኑ የተፈረመዉን የወደብ ኪራይ ስምምነትን አስመልክቶ በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል የተፈጠረዉን ዉጥረት ለማርገብ ያለመ እንደሆነም የአፍሪካ ህብረት መግለጫ ያሳያል፡፡

እስከዳር ግርማ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply