የአፍሪካ ህብረት የሲቪል እና ወታደራዊ መንግስቱ ችግሮቻቸዉን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጠየቀየህብረቱ ኮሚሽን ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ባወጡት መግለጫ በሱዳን ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በሰላማዊ…

የአፍሪካ ህብረት የሲቪል እና ወታደራዊ መንግስቱ ችግሮቻቸዉን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጠየቀ

የህብረቱ ኮሚሽን ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ባወጡት መግለጫ በሱዳን ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ አሳስቧል፡፡

አገሪቱን የሚታደጓት ዉይይትና መቻቻል ብቻ ናቸዉ ያሉት ሙሳ ፋኪ ማሃማት፤ የታሰሩት የሲቪል አመራሮች እንዲፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክንና ካቢኒያቸዉን ዛሬ ጠዋት በቤታቸዉ ዉስጥ ማሰሩ ተነግሯል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የአለም አቀፍ ተቋማትና አገራት በማዉገዝ ላይ ናቸዉ፡፡

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተቃዉሞ ሰልፎች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙ አልጄዚራና ቢቢሲ አስነብበዋል፡፡

አባቱ መረቀ
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply