የአፍሪካ ህብረት የጸጥታ ሃላፊዉ ገብረእግዚያብሄር መብራቱን ከሃላፊነት አነሳ፡፡ሜጀር ጀነራል ገ/ሄር መብራቱ ከሃላፊነት የተነሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር የታማኝነት ችግር አለባቸዉ የ…

የአፍሪካ ህብረት የጸጥታ ሃላፊዉ ገብረእግዚያብሄር መብራቱን ከሃላፊነት አነሳ፡፡

ሜጀር ጀነራል ገ/ሄር መብራቱ ከሃላፊነት የተነሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር የታማኝነት ችግር አለባቸዉ የሚል ቅሬታ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ተብሏል፡፡

በዚህም የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት የህብረቱን የጸጥታ ሃላፊ ከሃላፊነት ማንሳታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በፈደራል መንግስትና በህዋህት ቡድን መካከል እየተደረገ ባለዉ ጦርነት ሜጀር ጀነራሉ ለህብረቱም ሆነ ለሃገራቸዉ ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ለመወጣት ቁርጠኛ አይደሉም በሚል የመከላከያ ሚንስቴር ለህብረቱ ደብዳቤ መጻፉን ዘገባው ጠቁሟል።

በሙሉቀን አሰፋ
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply