የአፍሪካ ሳይንቲስቶች ስለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰጠውን አስተያያት ውድቅ አደረጉት

አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሳይንቲስቶችና የጤና ተሟጋቾች፣ የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ)፣ ለኮቪድ 19 የሚሰጠውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት መድሃኒትን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ በጣም ያሳዘናቸው መሆኑን ገለጹ፡፡

ሲዲሲ ባላፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫ የሞደርናና የፋይዘር ክትባት መድሃኒቶች፣ አልፎ አልፎ የደም መርጋት ወይም ከሱ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የሰውነት አካል መደንዘዝ ችግርን ሊያስከት ከሚችለው ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሻሉ መሆናቸውን ገልጾ ነበር፡፡ 

የደቡብ አፍሪካ የጤና መምሪያ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን በአፍሪካ በስፋት ከሚሰራጩ የክትባት መድሃኒቶች አንዱ መሆኑን ገልጾ አፍሪካውያን ክትባቱ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እንዲገንዘቡ አሳስቧል፡፡ 

የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰድ መድሃኒት መሆኑን በመጠቅሰ መድሃኒቱ በተለይ ሁኔታ ተጨማሪ ማቀዝቀዣ ውስጥ ማኖርን የማይጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ሲዲሲ በመግለጫው የክትባቶቹ ልዩነት የምርጫ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ የትኛውንም ክትባት መውሰድ ጨርሶ ካለመከተብ የተሻለ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ጤና ባለሙያዎች ግን የሲዲሲ መግለጫ ሁሉም ሰው እንዲከተብ በማድረግ ላይ ያሉትን ጥረት የሚጎዳባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአፍሪካ የተከቡ ሰዎች ቁጥር ከአጠቃላዩ ህዝብ 6 ከመቶ ብቻ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply