የአፍሪካ ኅብረት በኒዤር ቀውስ ላይ እየመከረ ነው

https://gdb.voanews.com/D106E1AB-B378-4C61-91DE-9B54672C18E8_cx0_cy5_cw0_w800_h450.jpg

የአፍሪካ ኅብረት፣ በኒዤር ቀውስ ላይ ለመነጋገር፣ ዛሬ ሰኞ፣ ዐዲስ አበባ ላይ ስብሰባ ተቀምጧል። “የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የጸጥታ ም/ቤት፣ በኒዤር ስላለው ወቅታዊ ኹኔታ እና ችግሩን ለመፍታት እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ ማብራሪያ ያደምጣል፤” ሲል፣ ኅብረቱ ቀድሞ ትዊተር፣ አሁን X ተብሎ በሚጠራው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ አስታውቋል።

በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት ውስጥ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የኒዤር ተወካዮች ይገኙበታል።

በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተነሡትን ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙምን አስመልክቶ፣ ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባለፈው ሳምንት ሲናገሩ፣ አያያዛቸው፥ “ተቀባይነት የሌለው ነው፤” ሲሉ፣ ኹኔታው “እጅግ አሳስቦኛል፤” ብለዋል።

ወታደራዊ ሁንታው፣ ትላንት እሑድ፣ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን የያዙትን ሞሐመድ ባዙምን፣ “በሀገር ክህደት” እንደሚከሥ አስታውቆ፣ የቀጣናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ(ኤኮዋስ)፣ በኒዤር ላይ የጣለውን ማዕቀብ አውግዟል።

ባዙም እና ቤተሰባቸው፣ ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በቤት ውስጥ እስር ላይ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply