የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ለ ሦስት ወራት ምርመራ ያደርጋል

የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ተባሉ የመብት ጥሰቶችን በይፋ መመርመር ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ምርመራ የፊታችን ሀሙስ ሰኔ 10 2013 በይፋ እንደሚጀምርም ከኮሚሽኑ የተገኘ መግለጫ ያመላክታል ሲል አል አይን ዘግቧል።

የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሥራውን በጋምቢያዋ ዋና ከተማ ባንጁል በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚጀምርም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በትግራይ ክልል መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላም የጎረቤት ሀገራትን ሁኔታ ለማየት እንደሚሞክር ነው የገለጸው።

ኮሚሽኑ ለሶስት ወራት ተቀምጦ ሁኔታውን እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ የሶስት ወራት ጊዜውም ሊታደስ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት እንዳለውም ገልጿል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 09/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

Source: Link to the Post

Leave a Reply