የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪዎች ቡድን በኮፕ 28 ስትራቴጂ አጀንዳ ላይ መከረ

አርብ የካቲት 10 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪዎች ቡድን በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት፣ በመጭው የኮፕ 28 ስብሰባ የአፍሪካን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ስትራቴጂ ላይ ምክክር አካሂዷል፡፡

የፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትህ አሊያንስ፣ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን በመሰብሰብ ለኮፕ 28 ስትራቴጂ ነድፏል፡፡ በአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማኅበበራትና ግብረሰናይ ድርጆቱ የተሳተፉበት ምክክር፣ የአፍሪካን የአየር ንብረት አቋም የአፍሪካ ተደራዳሪ ቡድን መጭው የኮፕ 28 ስብሰባ ቁርጠኛ አቋም ይዞ እንደሚቀርብም ተመላክቷል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደው የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ምክክር እና ስትራቴጂ ላይ በተደገው ንንግር፣ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የአፍሪካን ስኬት ለማረጋገጥ መሪዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ እና ሌሎች የልማት ድርድሮች እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካን አየርን ንብረት ለውጥ ግብ ለመሳካት የባለድርሻ አካላት ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

ተደራዳሪ ቡድኑ ባለፈው ዓመት በግብጽ በተካሄደው ኮፕ 27 ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ለማጠናከር መወሰኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ በከፕ 28 ሰብሰባ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ከባድርሻ አካላት የሚየገኛቸውን ግብዓቶች እንደሚተቀም ገልጿል፡፡

የሴቶች ተደራዳሪዎች በማበረታታት የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን በመደገፍ እና በአንድ ድምጽ ስምምነት ላይ በመመስረት፣ ሴቶች በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ግንባር ቀደም እንዲሆኑ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ድርድር ሂደት ውስጥ የአፍሪካ አጀንዳ እውን ለማድረግ፣ የአፍሪካ መንግሥታት የዓላማ አንድነትን ለማረጋገጥ በቴክኒካዊ ሂደቶች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

The post የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪዎች ቡድን በኮፕ 28 ስትራቴጂ አጀንዳ ላይ መከረ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply