#የአፍንጫ አለርጂ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሶች፤ ሰውነት ውስጥ ለሚገባ ባዕድ ነገር የሚሰጡት የመቆጣት ምላሽ አለርጂ ይባላል፡፡አለርጂ በአፍንጫ እና በሌሎች የመተንፈሻ አካላት ላይ ይከ…

#የአፍንጫ አለርጂ

የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሶች፤ ሰውነት ውስጥ ለሚገባ ባዕድ ነገር የሚሰጡት የመቆጣት ምላሽ አለርጂ ይባላል፡፡

አለርጂ በአፍንጫ እና በሌሎች የመተንፈሻ አካላት ላይ ይከሰታል፡፡ አንዳንድ የአለርጂ ህመሞች ከባድ ህመም የሚያስከትሉ እና አጣዳፊ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ተብሏል።

ዶክተር ብስራት ጌታቸው ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሃኪም ናቸው፤ የአፍንጫ አለርጂ አንድ ነገር ወደ አፍንጫ ሲገባ እና ሰውነት የተጋነነ ምላሽ ሲሰጥ አለርጂ ይባላል ብለዋል፡፡ አለርጂው ያስነሳው የአፍንጫ መቆጣት የአፍንጫ አለርጂ እንደሚባል ተናግረዋል፡፡

#የአፍንጫ አለርጂ መነሻ ምንክያቶች፤

• አቧራ
• ቅዝቃዜ
• ሙቀት
• ጭስ
• ኬሚካሎች
• በአንዳንድ ሰዎች ላይ መጥፎም ሆነ ጥሩ ሽታ ለምሳሌ እንደ ሽቶ ፣ እጣን ለአለርጂ ምክንያት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአፍንጫ አለርጂ ወቅት እየጠበቀ የሚነሳባቸው ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ባለሞያው ሁሌም ቢሆን በአንዳንዶች ላይ ለአለርጂ ተጋላጭ ከሆኑ ህመሙ እንደሚነሳባቸው ተናግረዋል፡፡

#ምልክቶች

• የአፍንጫ ፈሳሽ መዝረክረክ
• አይን አከባቢ መብላት ወይም ማሳከክ
• የአፍንጫ ማፈን እና ማስነጠስን
• ንጹ ፈሳሽ ከአፍንጫ መውጣት
• የአፍንጫ መድማት
• ጉንፋን መሰል ምልክቶች በታማሚው ላይ የሚስተዋሉ ይሆናል፡፡

#ህክምናው

በቅድሚያ ለአለርጂው ከሚያጋልጡ ነገሮች መጠንቀቅ እና አፍንጫን በውሃ እና በጨው ማጠብ እንደሚመከር ተጠቁሟል፡፡

በህክምናው ሰውነትን ሊያረጋጋ የሚችሉ መድሃኒቶች በሚዋጥ ኪኒን እንዲሁም አፍኝጫ ውስጥ በሚነፉ መድሃኒቶች ህመሙ የሚታከም መሆኑን ነግረውናል፡፡

#መከላከያ መንገዶች፤

ከጉፋን የሚለይበት መንገድ በህክምና ወቅት መሆኑን የሚናገሩት ባለሞያው፤ በተደጋጋሚ የሆነ ማስነጠስ፣ አይን አከባቢ ማሰከኩን እና አፍንጫ በመታፈኑ አማካኝነት በመጠኑ ሊለይ ይችላል ተብሏል፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት የአፍንጫ አለርጂ የሚቀሰቀስበት እንዲሁም ህመሙ ያለባቸው ሰዎች የሚቸገሩበት ጊዜ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ብስራት አለርጂውን ከሚቀሰቅሱ፤ አቧራ፣ ብናኝ ፣ ኬሚካሎች እና ሽቶዎች መጠንቀቅ እንደሚያስፈል እና ቀደም ሲል የተነገሩ ምልክቶችን የሚስተዋሉ ከሆነ ግን ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ይገባል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply