የአፍጋን ሴቶች የትምህርትና የሥራ መብታቸው እንዲከበር ጠየቁ

አፍጋኒስታን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሴቶች ዛሬ ማክሰኞ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አዲሱ የአፍጋኒስታን አመራር የሆነው ታሊባን ለሴቶች የትምህርትና የሥራ ዕድል እንዲፈቅድ ጠይቀዋል፡፡

ሴቶቹ በተቃውሟቸው ያሰሟቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል

“ትምህት ቤቶችን ለምን ዘጋችሁ፣ ሥራ ምግብና ትምህርት” የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

መንግሥታትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ታሊባን ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ካለፈው ነሀሴ ጀምሮ የሴቶችን መብቶች እንዲያከብር ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ታሊባን ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ ሴቶች ከሌላ ሰው ጋር ካልሆኑ በቀር ብቻቸውን ከ72 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው እንዳይጓዙ አዟል፡፡ 

የታክሲ አገልግሎት ሰጭዎችም የእስላሚክ ሂጃብ ወይም ራሳቸውን ለሸፈኑ ሴቶች ብቻ እንዲሰጡ መመሪያ ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply