የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ 189 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ገለጸ

የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ 189 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ 189 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ገለጸ።

በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይል አካል የሆኑት የኡጋንዳ ወታደሮች ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውን 189 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ በአንዱ ካምፕ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተክሎ ነው እርምጃ የተወሰደባቸው።

የኡጋንዳ ወታደሮች በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ(አሚሶም) አካል ሲሆኑ፤ ማዕከላዊ መንግስትን በመደገፍ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

የኡጋንዳ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮቹ ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 100 ኪሎ ሜትር ርቀው በሚገኙ ሲጋሌ ፣ አዲሞሌ እና ካይቶይ በተባሉ መንደሮች የአልሸባብ መደበቂያ ቦታዎችን መውረራቸውን ገልጿል ፡፡

የኡጋንዳ ጦር ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሎኔል ዲኦ አኪኪ ጥቃቱን ከመሬት እና ከአየር ላይ ማድረሱን ገልጸው፤ በዚህም በአንድ ቀን ውስጥ የተገደሉት የአልሸባብ ተዋጊዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንም ጠቅሰዋል ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ 189 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply