የኢህአፓ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/I8E1I3UCv05ukVtn8vPTG2rGoQHPWzs5idS5UP__wnpUUmc4gIwC2JvArv7wdXCclwqlAuZNglQTZ1KlMxePAB-Ksy4idHMSafiAG1T1_pTFwkqNfecj9C4a0afffTuAacV0F7o8NNItx-FWkiw0v34A0AwNX3v8GDD3Ume9_eSy3PDM0gb30ZhUoFHsRgAmVrDs-gJbcPfbarpVJRWsUyMGbLOEFmB6S9HLZuis9ktcWkp90w0YWjW_nrqutnsSw3HroorcjV3rlEKY2xqoOnN2Q5nOj_sIGF3-4FE_sQaPxMGyXgYzWKN8KnCv-VAHcSsI1dY2N5EUYu7TqT6lsg.jpg

የኢህአፓ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ማለዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሀይማኖት ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታም ሊቀመንበሩ በቢሯቸው በስራ ላይ እያሉ በፖሊስ መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡

እስከዚህ ሰዓት ድረስም በ3ኛ ፖሊስ ጣብያ እንደሚገኙ ከምክትል ሊቀመንበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሊቀመንበሩ በአዲስ አበባ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን በምን ጉዳይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply