የኢህአፖዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ አብርሃም ሃይማኖትን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞች ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ባለፈዉ ህዳር 30/ 2016 ዓ/ም ”’ ጦርነት ይቁም ሰላ…

የኢህአፖዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ አብርሃም ሃይማኖትን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞች ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

ባለፈዉ ህዳር 30/ 2016 ዓ/ም ”’ ጦርነት ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል በአዲሰ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ታስቦ እንደነበር ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ ሦስት የሠልፉ አስተባባሪዎች የነበሩት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት፣አቶ ናትናኤል መኮንን እና አቶ ጊደና መድህን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸዉ ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ አበራ ንጉስ ፍርድቤቱ ሐሙስ 05/07/16 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት የታሰሩት ከህግ ዉጭ በመሆኑ እንዲፈቱ ሲል ለፌደራል ፖሊሰ ትእዛዝ መስጠቱን ነግረዉናል።

ፓለቲከኞቹ ባለፍት ሁለት ቀናት ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም እስካሁን እንዳልተለቀቁና ፍርዱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተስፋቸዉን ገልፀዋል።

በቁጥጥር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ ፍርድ ቤት ቀርበዉ የማያዉቁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በፌደራል ፖሊስ እጅ መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን የአካል ነፃነታቸዉ እንዲከበር ሲከራከሩ ቆይተዉ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቱ ወስኗል ብለዉናል።
የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት 05/07/16 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ አመልካቾች የአካል ነፃነታቸዉ እንዲያከብር ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያዉ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ትዕዛዝም ፌደራል ፖሊስ የከፍተኛዉ ፍርደ ቤት ዉሳኔን በማክበር ከእስር በመልቀቅ ምላሽ በፅሁፍ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የአስተባባሪዎቹ ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ አበራ ፌደራል ፖሊስ ይህንን የማይሻር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲያከብር ጠይቀዋል።

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply