የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ለጊዜው አዲስ ፓስፖርት መስጠት ማቆሙን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም       አዲስ…

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ለጊዜው አዲስ ፓስፖርት መስጠት ማቆሙን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ለጊዜው አዲስ ፓስፖርት መስጠት ማቆሙን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኤጀንሲው እንዳስታወቀው በዋናው ዳታ ቤዝ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ለጊዜው ማቆሙን ገልጿል። በመሆኑ ደንበኞች ኤጀንሲው ባጋጠመው የሰርቨር ችግር ምክንያት የተቋረጠው አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈቶ ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንስኪመለስ በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡ የኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስታዳደር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ኤጀንሲው ካጋጠመው የሰርቨር ችግር ውጪ በድረ-ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት አልተቋረጠም ብለውናል፡፡ በኤጀንሲው ዋና ሰርቨር ላይ ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ በመግባት ቀጠሮ ማያዝ እንደሚችሉ አቶ ፍራኦል ነግረውናል። ያጋጠመውን ችግር ዛሬ ወይንም ነገ አልያም በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየሰራ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ዘገባው የኢትዮ መረጃ ኒውስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply