የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።የፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚር አብዶላሂ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/X6MByQoR2_VvDJCBXxKv4YuCaqO9bSpbdNftcxVO18tuYx-J_ujYB78mbDRgdAe7ngueKongtcHdvrOrPvYUsAOYEfmgeWtO2YUhgQi-Koj5xr88BeqkmE2u_BMMUFfKy1dGmD9iI3owDs9JnYstY6HFbblxg0yTpRmYERt7NXB3huStqq2MvnNP021sJ5wUSCyXeBx_QOGc8B5Cwn4vZHHS1OspNBpJTmiPHYAYvzfdJ-ZuQlowgT9T-iHvKxN6_UOUVzTpz6BU82XcFDc7dZVuDFSwxFqh_DfWdgNBV8drwNytsj2ckiBQEeEM5COSBsMVxpI8fc9cNMc-qtwKQg.jpg

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

የፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚር አብዶላሂ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

በትናንትናው ዕለት በደረሰው የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ አራት ሰዎች መሞታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

ፕሬዚዳንቱ ኢራን ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የተገነቡ ሁለት ግድቦችን አስመርቀው ወደ ታብሪዝ እያመሩ ነው አደጋው ያጋጠማቸው፡፡

ሄሊኮፕተሩ ከታብሪዝ ከተማ 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እክሉ የገጠመው ሲሆን በቦታው የነበረው ጭጋጋማ የአየር ንብረት ለነብስ አድን ቡድኑ አስቸጋሪ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ከፍለጋዎች በኋላ ፕሬዝዳንቱን እና ሚኒስትሩን ያሳፈረው ሄሊኮፕተር ተራራማ እና በረዷማ በሆነው አካባቢ  ሲገኝ የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት እንደነበርም ነው የተገለፀው፡፡

ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply