የኢራኑ ፕሬዚዳንት የሄሊኮፕተር አደጋ ደርሶባቸው ያሉበት ሁኔታ  አይታወቅም ተባለፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር አደጋ ማስተናገዷን ተከት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/voLFP5a1tj9Hbxoj-nb8nR2IpjeLnyrb2v02iIVKyaUDRzdaIomRsRpLVRcTKCKqLjd2ICdMo_Zb5fZmuRsG4Vvm93CE0Wa_UVB09rcHrgfuIUdhU9ma5Vd1vuKBoJXawojkWxT2ICcVd5Jsq9FrFxxVKHNzTqNiqiwwRaxmHu3dykGVBQ4dsPiydjcUbZZmKyHOuAUB3n8fx0tvw7Ugz9BYngDSTkVQNLD0Kz-ZB9HoIr1HH4oAiacSRDYIaszdcGasGZFfHiEu9l2lv7vjOPE15boIRhyDEaFu0n9ZBYIpBLc3gIlnHvY4Hu1XrUAG5_8ZuaJW3WJQeYa7DcnEEQ.jpg

የኢራኑ ፕሬዚዳንት የሄሊኮፕተር አደጋ ደርሶባቸው ያሉበት ሁኔታ  አይታወቅም ተባለ

ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር አደጋ ማስተናገዷን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ አደጋ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

በሰሜናዊ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በደረሰው አደጋ ፕሬዚደንቱ የተሳፈሩባት ሄሊኮፕተር ለማፈላለግ ጥረት እየተደረገ ነው ።

ፕሬዝዳንቱንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ያሳፈረችው ሄሊኮፕተር ተራራ ጋር መጋጨቷም ተገልጿል።

ሁሉም ኢራናዊ ለፕሬዚዳንት  ኢብራሂም ራይሲ ፀሎት እንዲያደርግ ጥሪ መተላለፉንም ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በአባቱ መረቀ

Source: Link to the Post

Leave a Reply