የኢራን ሚሊሻዎች በሶሪያ ዳግም መስፈራቸው ተሰምቷል፡፡

የኢራን ሃይሎችና ታማኝ ታጣቂዎች ዳግም በምስራቃዊ የሶሪያ ግዛት መስፈራቸው ተነግሯል፡፡ባለፈው ረቡዕ በምስራቅ ሶሪያ ከባድ የአየር ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል በዚያ ጥቃት ከስፍራው የራቁት ታጣቂ የኢራን ሚሊሻዎችና በኢራን እንደሚደግፉ የሚነገርላቸው ሃይሎች ስፍራውን ጥለው መፈርጠጣቸው ይታወቃል፡፡

በዚያ የባለፈው ረቡዕ የእስራኤል ነው በተባለለት የአየር ጥቃት በትንሹ 57 ሰዎች መገደላቸውም ይታወቃል፡፡ከሟቾቹ ብዙዎቹ ደግሞ በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎች ናቸው ሲል የዘገበው አሻርቅ አል አውሳት ነው፡፡

ቀን 08/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply