የኢራን ሴቶች ማህበር “አትግደሉን” በሚል ርዕስ በበርሊን ከተማ ባዘጋጀው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በሴቶች እና በህጻናት ሰብአዊ መብት ዙሪያ በመስራት የምትታወቀው ሀያት መሀመድ እና ደጀን የበ…

የኢራን ሴቶች ማህበር “አትግደሉን” በሚል ርዕስ በበርሊን ከተማ ባዘጋጀው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በሴቶች እና በህጻናት ሰብአዊ መብት ዙሪያ በመስራት የምትታወቀው ሀያት መሀመድ እና ደጀን የበርሊን አማራዎች ተሳትፈዋል፤ በእለቱም በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት በማውገዝ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢራን ሴቶች ማህበር በኢራን የተለያዩ አካባቢዎች በሴቶች እና በህጻናት ላይ እየተፈጸመ ነው ያሉትን ግድያ “አትግደሉን” በሚል ርዕስ በጀርመን ሀገር በርሊን ከተማ ታህሳስ 1/2015 ( Dec.10/2022) ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተው ነበር። በዚህ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍም በሴቶች እና በህጻናት ሰብአዊ መብት ዙሪያ በመስራት የምትታወቀው ሀያት መሀመድ እና ደጀን የበርሊን አማራዎች በመሳተፍ በኢትዮጵያ በተለይም ኦሮሚያ በሚኖሩ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት አውግዘዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ወለጋ እና አካባቢው በሴቶችና በህጻናት ላይ የሚፈጸመው እልቂትም የከፋ መሆኑን ለማሳዬትም በግፍ የተገደሉ ሴቶችና ህጻናትን ፎቶ በባነር በማሰራት አደባባይ ይዘው ወጥተዋል። Stop Amhara Genocide/በአማራ ላይ የሚፈጸመው የዘር ፍጅት ይቁም! የሚል መልዕክት በጀርመንኛ እና በእንግሊዝኛ በበባነር ላይ በመጻፍ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚህ ሰልፍ ላይ ከሀያት መሀመድ በተጨማሪም:_ እነ ኢንጅነር መኳንንት፣ ወሰኑ፣ ቅጽላ፣አያልነህ፣ ቅድስት እና ሌሎችም በአማራው ዙሪያ በትኩረት የሚሰሩ ወገኖች ተገኝተው መንግስት መር በሆነ መልኩ እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ እና እየተሳደዱ ለሚገኙ አማራዎች ድምጽ ሆነዋል። በበርሊን በእግር ከአራት አቅጣጫ ተነስተው በመሰባሰብ በተለይም ከተገናኙበት ከብራንግ በርቱዋ ወይም አለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ከሚካሄድበት አካባቢ በመነሳት ወደ ቡንዲግስታግ ወይም የጀርመን የፓላማ መቀመጫ አካባቢ በማቅናት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በግፍ የተገደሉትን የሰማዕታትን ፎቶ ግራፍ በባነር አሰርተው በመያዝ እንዲሁም በሻማ ማብራት ስነ ስርዓቱ ተሳትፈዋል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው የታጠቁ አካላት በሰላማዊ አማራዎች ላይ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀዬ እያፈናቀሉ በማሳደድ እና በጅምላ በማጥቃት እያደረሱት ያለውን ኢሰብአዊ እና አሰቃቂ ወንጀል በቀጥታ ከወለጋ እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በምስል እና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደሚደርሳት ነው ሀያት መሀመድ ያስታወቀችው። በመሆኑም በጉዳዩ ላይ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ የሰው ልጅ ጉዳይ ይገደናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ ትኩረት እንዲሰጡት፣ እንዲያወግዙትና ለጉዳዩም አስቸኳይ የጋራ መፍትሄ እንዲፈልጉለት ስትል በአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጥሪ አድርጋለች። ከወለጋ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ማሻ ከተማ የሚኖሩ ከ7 ሽህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችም ከሰሞኑ በማሻ ከተማ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት በማውገዝ በገዳዮች ከበባ ስር ላሉ ወገኖቻችን የድረሱላቸው ጥሪ ማድረጋቸውን አውስታለች። ታህሳስ 2/2015 በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የበርሊን አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በሻማ ማብራት ንጹሃን ሰማዕታትን የሚዘክሩ አማራዎች እንዳሉም ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply