የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶሪያ ገቡ፡፡የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ገብተዋል።የፖለቲካ እና የፓር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/UtRkJQcFsF-LGT-RWjSd1yPt5gGpuwA5cmeY0bc6br-MBcMFavp8epSajk3sUxtpJx-hzzjqEl82Piotj8lBvbFMLENfv4ARyfirlW_95nQnaQnVpCeugssXXWUNoEYaOExMQrYskenRiJ0trpDM1MNmLffL3FgrotjJ7iJ--J-DAXTcgE_nx_V4f9drJjLrDuexxUJ0YBV0mwLgfYB89BG2kIlNsfzDwaKIwkNzwFahvRKEP1Vr7Y5FzjFMY0pLlz-3e2mSrGhg0Ajb9TMZj_chTl4f12VEKpfZyh95G0WRJHARk1EHH4dRwfsXGjtJeYJkIOQrbDbPkAHbUi-Uvg.jpg

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶሪያ ገቡ፡፡

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ገብተዋል።

የፖለቲካ እና የፓርላማ ልዑካንን በመምራት የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኦማን ዋና ከተማ ሙስካት ካደረጉት የክልላዊ ጉብኝታቸው በተጨማሪ በሁለተኛ ዙር ደማስቆ መግባታቸው ተሰምቷል።

ዲፕሎማቶቹ በደማስቆ በሚኖራቸው ቆይታ ስለጋራ ግንኙነት እና ስለአካባቢው ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በጋዛ ሰርጥ ስላለው የእስራኤል ጦርነት ለመወያየት ቀጠሮ እንደያዙ ተዘግቧል።

ጉብኝቱ የሚደረገውም በደማስቆ በሚገኘው መዜህ ሰፈር በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ቆንስላ ፅ/ቤት ላይ እስራኤል ከፈጸመችው ጥቃት ከቀናቶች በኋላ ነው።

በዚያ ጥቃት ሰባት የኢራን እስላማዊ አብዮት ከፍተኛ ጠባቂዎች ሃይል መገደላቸዉ ይታወሳል።

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply