የኢሰመጉ ማሳሰቢያ

በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን ደህንነት እንዲሁም የሲቪል ንብረቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ፡፡

ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና መላው ኢትዮጵያዊያን ግጭቱ ተባብሶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ ጉባኤው አሳስቧል፡፡

መንግሥት በየጊዜው ተከታታይ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጉባኤው ጠይቋል፡፡

የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና ብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች የሐሰት ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም ኢሰመጉ ጠይቋል፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply