You are currently viewing የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ!! “በሕግ ጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ መብታቸው ይከበር!”  ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) የኢትዮጵ…

የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ!! “በሕግ ጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ መብታቸው ይከበር!” ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) የኢትዮጵ…

የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ!! “በሕግ ጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ መብታቸው ይከበር!” ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ- ኢሰመጉ ላለፉት 30 ዓመታት ሲያከናውን ከቆየው ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብቶች ሥራዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትልና ምርመራ እንዲሁም የፍርድ ሂደት ክትትል ስራዎች ይገኛሉ፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ላይ የቀረበውን ክስ እና ከጅምሩ እስከ አሁን ያለውን የፍርድ ሂደት በችሎት በመታደም እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በዚህም የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ በሕግ ጥበቃ ሥር በሚገኙበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ በእስረኞች ተደብድበው አይናቸው አካባቢና ጉልበታቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከደረሱት መረጃዎች እንዲሁም በዕለቱ ፍርድ ቤት ቀርበው ከነበሩትና ጉዳት መድረሱን ለችሎቱ ከገለፁት የማረሚያ ቤቱ የፈረቃ ኃላፊ ቃል ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም እስረኛው እስከ አሁን ሕክምና እንዳላገኙ፣ ከዚህ ቀደም ከአቶ ስንታየው ቸኮል ጋር በመሆን አሁን ጥቃቱን የፈፀሙት እሰረኞች ለደህንነታቸው እንደሚያሰጓቸው ገልፀው ለማረሚያ ቤቱ ማመልከታቸውን፣ በዚህም አስረኞቹ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ የተደረገ ቢሆንም ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመገንዘብ ችሏል፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው በቀን 19/01/2014 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር ባ/ለ/ዴ/0351 ለኢሰመጉ ባቀረቡት አቤቱታ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ስንታየው ቸኮል የኩላሊት ህመም ያጋጠማቸው መሆኑን እና በዚህም የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ማረሚያ ቤቱን ጠይቀው አገልግሎቱን ለማግኘት አለመቻላቸውን ገልፀዋል፡፡ ኢሰመጉም እስረኛው በሕጉ ያላቸውን መብት ጠቅሶ፤ ሕክምና እንዲያገኙ ያልተደረገበትን ምክንያት በተመለከተ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የፅሁፍ ማብራሪያ እንዲሰጠው በቀን 27/1/2014 ዓ.ም፣ በቁጥር EHRCO/CE/002/2014 በተፃፈ ደብዳቤ ጠይቆ መልሱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል.. .ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply